የሀብት መሠረት

የሀገራት ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገትና በልማት የመበልጸግ እጣ ፋንታ ሀገራቱ በሚኖራቸው መነሻ ሀብት፣ እንዲሁም እነዚህን ሀብቶች ወደ ልማት ለመቀየር በሚኖር አቅም ይወሰናል፡፡ በመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት ከሚስተዋሉ ክስተቶች መካከል አንዱና ዋናው ማሕበረሰቦች ዋና የሀብት አቅማቸውን ተፈጥሮ ከለገሰቻቸው መሬትና ማዕድን ወደ ሰው ሠራሽ ቁሳዊ ካፒታል፣ ከቁሳዊ ካፒታል ወደ ሰብዓዊ ካፒታል እንዲሁም ከሰብዓዊ ካፒታል ወደ ማሕበራዊ ካፒታል መቀየር በቻሉ ቁጥር የኢኮኖሚ ዕድገት ምንጫቸውም ከውሱን ግብርና ወደ ኢንዱስትሪና ዓለምአቀፍ አገልግሎት ይዘምናል፡፡ ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ትኩረት በመስጠት እውቀት መር ኢኮኖሚን ለማረጋገጥና በአጠቃላይ የመዋቅራዊ ሽግግር ለማስፈን መትጋት ከጀመረች ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ለዚህ ሂደት መሳካት ቁልፉ ግብዓትና የሂደቱ ተጠቃሚ ሰው በመሆኑ ይህን ሀብት ለማነጽ በአለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ለትምህርትና ለጤና ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ ከፍተኛ ሥራ ተከናውኗል፤ አበረታች ውጤትም ተገኝቷል፡፡

በሌላ በኩል ላለፉት አሥርት ዓመታት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረገውን የአገልግሎት ዘርፍ በመዋቅራዊ ሽግግር አግባብ የዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ምንጭ ማድረግ የሚቻለው ዘርፉን በንግድና በቱሪዝም ሥልቶች ዓለም አቀፍ የእሴት ሰንሰለት ውስጥ በማስገባት ጭምር ነው፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ብዙም ያልተጠቀመችበት አንዱ ትልቁ አቅሟ የቱሪዝም ሀብቷ ነው፡፡

የሀገሪቱ ክልሎች እንደ ሀገሪቷ ማህበረሰቦች ሁሉ ዓይነተ ብዙ የሆኑ የተፈጥሮና የሰው ልጅ አሻራ ያረፈባቸው ቁሳዊና ሰብዓዊ ሀብቶች አሏቸው፡፡ ከዚህ አንጻር የሐረሪ ክልል ለአለፉት ዘመናት የሥልጣኔ መዳረሻ፣ ለቀጣይ ልማትም መነሻ የሚሆን ትልቅ ሀብት አለው፡፡ የሰብዓዊ ካፒታል አንዱና ዋናው የሐረሪ ክልል ሀብት ነው፡፡ የሐረሪ ጥንታዊነትና ታሪካዊነት፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ የካበቱ ባሕላዊ እሴቶች፣ የከተማ ልማት ልምዶችና የማሕበረሰቡ የቆየ የንግድ ባሕል ለሐረሪ ክልል ልማት ጉልበት የሚሆኑ ትልቅ የሀብት ምንጮች ናቸው፡፡

Read 842 times

ሀረሪ ክልል ከተማ

ሀረሪ ሕዝብ ክልል ራሱን በራሱ ባስተዳደረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት ተኩል አመታት የክልሉን ሕዝብ ቋንቋ ፣ ባህል እና ቅርስ ለማስተዋወቅ ፣ ለመጠበቅ እና ለማሳደግ የጣረ ሲሆን የዚህ በዓል በክልሉ መከበር እነዚህን ግቦች በበለጠ ሁኔታ ለማሳካት ትልቅ በር ከፍቶለታል፡፡

ክቡር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ

Contact Us!

  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
  +251 466 0563
  +251 466 0268
  90 Harar

Keep in Touch