Thursday, 15 August 2019 12:19

በጤናው ዘርፍ ያሉ የአፈፃፀም ልዩነት ከመቅረፍ አንፃር የአመራር ቁርጠንነት አስፈላጊ ነው-የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ፡፡

Rate this item
(0 votes)

የሀረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የ2011 የበጀት አመት አፈፃፀም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየገመገመ ነው፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት መንግስት ባለፉት አመታት ተላላፊ በሽታዎችን በተለይም ወባን፣ቲቢንና ኤች አይ ቪ ኤድስ ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ሞትን ከመቀነስ አንፃር አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ከእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አራት አጀንዳዎች ለማሳካትም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፣በተለይም የወረዳ ትራንስፎርም ለማድረግ ሰፊ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡

በወረዳዎች መካከል በጤናው ዘርፍ ያሉ የአፈፃፀም ልዩነት ከመቅረፍ አንፃር የአመራር ቁርጠንነት አስፈላጊ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአፈፃፀም (ልዩነት) ክፍተቶችን ከመቅረፍ አንፃር ትኩረት ሰጥቶ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በእለቱ የተጀመረው ግምገማ ከአመለካከት ከክህሎት ከግብዓት አንፃር ያሉ ክፍተቶችን መለየትና ለዝግጅት ምዕራፍ እንደ ግብዓት መውሰድ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከአሰራር በአደረጃጀት መታረም ያለባቸው ዋና ዋና ማነቆዎችን ተለይተው ለዝግጅት ምዕራፍ መጠቀም መቅረፍ አስፈላጊ መሆኑን አመለክተዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብሳ ኢብራሂም በበኩላቸው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በመጨረሰሻ አመት ላይ እንገኛለን ስለሆነም የአራተኛውን አመት አጠቃላይ ግምገማ ጠንካራ ጎኖች በማጠናከርና የነበሩ ውስንነቶች በማስተካከል የምንሰራበት አመት ከመሆኑ አንፃር የሚመለከተው አካል ሁሉ ትኩረት ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ ጠይቀዋል፡፡

በመድረኩም የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና አባላት፣ካቢኔዎችና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ጤና አስተባባሪዎች የተቋማት ሃላፊዎች፣አጋር ድርጅቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read 373 times