Friday, 16 August 2019 14:21

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2011 በጀት አመት የካፒታል ፕሮጀክት እና የ SDG በጀት አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ።

Rate this item
(0 votes)

የክልሉ መስተዳደር ም/ቤት (ካቢኔ) በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ በገንንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የቀረበውን የ2011 በጀት አመት የካፒታል ፕሮጀክትና የ SDG በጀት አፈፃፀምን የክልሉ አመራር አካላት በተገኙበት ገምግሞ ሪፖርቱን አፅድቋል።

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በቀረበው ሪፖርት መሰረት አጠቃላይ በ2011 በጀት አመት በካፒታል ፕሮጀክትነ ብር 1,053,145,405 እንዲሁም በ SDG በጀት ብር 45,000,000 ተመድቦ የነበረ ሲሆን አጠቃላይ የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀሙም አማካኝ:-
* ጥቅል ፋይናንሺያል አፈፃፀም በአማካኝ 64% ሲሆን
* ጥቅል ፊዚካል አፈፃፀም በአማካኝ 54% እንደሆነ በሪፖርቱ የቀረበ ሲሆን ይህ አፈፃፀምም ከባለፈው 2010 በጀት አመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀርም የተሻለ አፈፃፀም እንደሆነ ተገልጧል።

የመስተዳደር ም/ቤቱ ሰብሳቢና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት የዘንድሮው የ2011 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት እስከ ታህሳስ በክልሉ የነበሩ የተለያዩ አጀንዳዎችንና ችግሮችን በመፍታት ላይ ያተኮረ እንደነበርና የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች በአጥጋቢ ሁኔታ አለመከናወኑን በመጠቆም የዘንድሮው የ2011 በጀት አመት አፈፃፀም ከባለፈው 2010 በጀት አመት ጋር ሲነፃፀርም ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይም ከአመራር አካላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በቀጣይ ሳምንትም የሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የወረዳ መስተዳድሮች የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እንደሚካሄድ በክልል ደረጃ ለ2012 በጀት አመት የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች በበቂ ሁኔታ መከናወን እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።

Read 412 times